ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 385 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

0
451

ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 385 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 572 ሴቶችንና 112 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 385 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው መግባታቸው ተገልጿል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ ተገቢው አቀባበል እንደተደረገላቸው ታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here