በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመ መሆኑን ኤርትራ አስታወቀች

0
507

በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የኤርትራው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አስታወቁ።

አቶ የማነ እንደገለጹት፤ ህወሓት በስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ባሉ ንጹሃን ኤርትራዊያን ላይ ሳይቀር በበቀል ተነሳስቶ ጭፍጨፋ እየፈጸመ ይገኛል።

ህወሓት እየፈጸመ ያለው የበቀል ግድያና ጭፍጨፋ ብሎም የድርጅቱ ህገ ወጥ ተግባራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ባሉ ኤጀንሲዎች እና የድርጅቱ አፍቃሪ መገናኛ ብዙሀን ቸል መባሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በጄኔቫ የኤርትራ ኤንባሲ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረትም ትግራይ ክልል ባሉ የስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ኤርትራዊያን እየተገደሉ ይገኛሉ።

በጄኔቫ ያሉት የኤርትራ አምባሳደር በዚህ ጉዳይ ላይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ጋር መነጋገራቸውን ኤንባሲው አስታውቋል።

ከዚህ መረጃ በፊትም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ያሉ ንጹሀን ዜጎች የደህንነት ስጋት እንደተጋረጠባቸው ጠቅሶ ስጋቱን ማስተወቁ አይዘነጋም።

በተመሳሳይመ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን ንጹሀን ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት መጋለጣቸውን ማስታወቁ እንዲሁም ከሳምንት በፊት በክልሉ የተወሰኑ አካባቢዎች አገልግሎት መስጠት ማቆሙን መግለጹ ይታወሳል ሲል የዘገበው የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here