በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰ

0
938

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡

የወራቤ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ አደጋ መከላከል ቁጥጥር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ምክትል ሳጅን ቢላል አወል ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰዓት ገደማ ካሊድ ወንዝ ላይ ኤፍኤስ አር ሲኖ ትራክ እና ባለሶስት እግር ባጃጅ ተጋጭተው አደጋው አደጋው መድረሱን አስታውቀዋል።

በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

የአደጋው ተጎጂዎች በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን አስተባባሪው መናገራቸውን ከደቡብ ክልል መንግሥት ኮሚሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here