በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንድ ጀምበር 7 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ

0
437

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሐምሌ 8/2013 ዓ.ም 7 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ሚኒስትሮች፣ የክልሉ ፣ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአሶሳ ወረዳ መንገሌ 38 ቀበሌ ሐምሌ 02/2013 ዓም በይፋ መጀመሩ ይታወቃል።

“ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ-ሃሳብ በሚከናወነው 3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 72 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ መያዙን ቢሮው ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ክረምት የሚተከሉ ችግኞች 28 ሺህ 881 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት እንደሚሸፍኑም ታውቋል፡፡

በክልሉ ሐምሌ 8/2013 ዓ.ም በአንድ ጀምበር ብቻ 7 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የገለጸው ቢሮው፣ ለዚህም የክልሉን ደን ለማሻሻል የሚያስችሉና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መዘጋጀታቸውን አመልክቷል፡፡

ህብረተሰቡ በዘመቻው ላይ ተገኝቶ አረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍም ቢሮው ጥሪ ማቅረቡን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here