ህግ የተላለፉ ከ1ሺህ በላይ አሽከርካሪዎችን መንጃ ፍቃድ አግጃለሁ፡- የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

0
661

ህግ በመተላለፍ ከባድ ጥፋት አጥፍተዋል ያላቸውን የ1ሺህ 117 አሽከርካሪዎች መንጃ ፍቃዳቸው ማገዱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

መንጃ ፍቃዳቸው የታገደባቸው አሽከርካሪዎች 290 ሞት፣ 827 ከባድ ጉዳት ያደረሱ በመሆናቸው ነው መንጃ ፍቃዳቸው የታገደባቸው ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የደህንነት ቀብቶን እና የህጻናት የደህንነት መደገፊያ በአሽከርካሪዎች መተግበሩን ለማጠናከር በተደረገው ቁጥጥር 4 ሺህ 443 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የቢሮው የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ስልክ እየተነጋገሩ ሲያሽከረከሩ የነበሩ 10 ሺህ 330 አሽከርካሪዎችና ከፍጥነት በላይ በአሽከረከሩ 1 ሺህ 20 አሽከርካሪዎች ላይ ላይ ቢሮው እርምጃ መወሰዱንም አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተብሎ ለብቻው በቀለም በተለዩት ከሜክሲኮ -ጀርመን፣ ከሜክሲኮ- ስታዲየም፣ ከለገሀር ፒያሳ፣ ከአንበሳ ጋራዥ ጎሮ እና ከላምበራት -ወሰን -ካራ ያሉ መስመሮችን ደንብ የማስከበር ተግባር ህጉን ተላልፈው በተገኙ 9 ሺህ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡

በሶስት ምልክትና ማመላከቻዎች (መቆም የሚከለክል፣ ዩ ተረን የሚከለክል፣ አስገዳጅ ምልክት) ለማስከበር በተደረገው ጥረት ህግ ተላልፈው በተገኙ 30 ሺህ 011 አሽከርካሪዎች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም 755 አሽከርካሪዎች የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ወደ ተቋም የተላኩ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እግዳቸውን ያጠናቀቁና ስልጠና ወስደው የተመለሱ 437 አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃዳቸው ተመላሽ እንደተደረገላቸውም ታዉቋል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here