ከከሰል ጋር ተመሳስሎ አውሮፓ እንዲገባ የተዘጋጀው ኮኬይን ተያዘ

0
530

ከከሰል ጋር ተመሳስሎ አውሮፓ እንዲገባ የተዘጋጀውና ከ41 ሚሊየን ዶላር በላይ ግምት ያለው ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ እጽ መያዙን የአየርላንድና ሆላንድ ደህንነት ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል።

መነሻውን ደቡብ አሜሪካ በማድረግ በሁለት እቃ ጫኝ መርከቦች ተጓጉዞ ሆላንድ ሮተርዳም ወደብ የደረሰው ኮኬይኑ የአየርላንድ የደህንነት ሰዎች ከነበራቸው ጥርጣሬ በመነሳት ምርመራ ማድረጋቸውን ተከትሎ መገኘቱን የአየርላንድ ፖሊስና ደህንነት አገልግሎት ገልጿል።

ለኤክስ ሬይ ማሽኖችና ለፖሊስ አነፍናፊ ውሾች ምስጋና ይድረስና ኮኬይኖቹ በ2ሺህ ከረጢቶች ከከሰል ጋር ተደባልቀው ተሞልተው የተገኙ ሲሆን ከሰሉን ከኮይኑ ለመለየት ቀናት እንደሚወስድ የአየርላንግ ፎረንሲክ ሳይንስ መስሪያ ቤት መናገራቸውን ሲኤን ኤን ዘግቧል።

ኮኬይኑ የተጫነበት መርከብ ሮተርዳም የደረሰው ከሳምንት በፊት ሲሆን ምርመራው እንደተጠናቀቀ የመርከቡ ሰራተኞች ወደ እስርቤት ይላካሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው አስነብቧል።

የምርመራ ውጤቱ የተደራጀ ወንጀልና የአደንዛዥ እጾች ዝውውር ውስጥ ያሉና ኑሮዋቸውን በአየርላንድ ያደረጉ ሰዎችን ለመልቀም የሚያስችል መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን የሃገሪቱ ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ጆን ኦድሪስኮል መናገራቸውም ተገልጿል።

ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነሩ ሃሳባቸውን ሲቀጥሉ ተመሳሳይ ወንጀሎችን ለመከላከልና በአውሮፓ ማህበረሰብ ዘንድም ተገቢው የህግ ማስከበር እንዲኖር ካስፈለገ አለም አቀፍ ትብብር ማድረጉ ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ክስተቱ የአውሮፓ ህብረት በተደራጁ የወንጀል ቡድኖች ላይ ሊወሰድ ስለሚገባው አስፈላጊ የመከላከልና የማስወገድ እርምጃ እንዲያስብበት ለማድረግ መነሻ ሊሆነው እንደሚችል ያስነበበው ዘገባው ተመሳሳይ ክስተቶች በአውሮፓ እየተደጋገሙ መምጣታቸውን ስፔንን ለማሳያነት አቅርቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here