“አዲስ ስታንዳርድ” የተሰኘውን የኦንላየን ሚድያ ታገደ

0
822

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በኦንላየን ሚድያነት ተመዝግቦ ሲሰራ የነበረውን “አዲስ ስታንዳርድ” የተሰኘውን ሚድያ በጊዜያዊነት ማገዱን አስታውቋል።

ሚድያው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሀት ሽብርተኛ ቡድን ስለመሆኑ ያስተላለፈውን ውሳኔ ባለመከተል እና የሽብርተኛ ቡድኑን አጀንዳ ማስፈፀሙን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባደረገው ክትትል የደረሰበት መሆኑን ነው የገለፀው።

በምክር ቤቱ ሽብርተኛ ቡድን ብሎ የተሰየመውን አካል የምክር ቤቱን ውሳኔ በመተላለፍ እንደ ህጋዊ የጦር ኃይል መጥራት እና ሌሎች ተመሳሳይ የህግ ጥሰቶች ተጨማሪ ክትትል እንደሚካሄድባቸው እንዲሁም እርምጃ እንደሚወሰድም ነው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የገለፀው።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለፕሬስ ነፃነት ያለውን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሰ ጋዜጠኝነትን እንደሚያበረታታ በመግለጫው አስታውቋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንደ ሚድያ ተቆጣጣሪ አካል ነፃነት ከኃላፊነት እና ከተጠያቂነት ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ መሆኑን በማስታወስ ሁሉም ሚድያዎች የህግ የበላይነትን አክብረው በኃላፊነት እንዲሰሩ ማሳሰቡም ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here