የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ ሽያጭና ስጦታን የሚመለከቱ አገልግሎቶችን በጊዜያዊነት አገልግሎት መስጠት ማቋረጡን አስታውቀ፡፡
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአዲስ አበባ የውክልና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን አሰራር ለማሻሻል እና ዘመናዊ ለማድረግ፣ ተቋሙ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በተመለከተ የሽያጭና ስጦታን አገልግሎት ለተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን ተከትሎ አገልግሎቱ የተቋጠበትን ምክንያት የኤጀንሲውን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ አስረድተዋል፡፡
አቶ ሙሉቀን እንዳሉትም በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በጋራ ለማቀናጀትና የዳታ ሲስተሙን በተሻለ መልኩ አንድ ላይ ለማጣመር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ በመሆኑ አገልግሎቱን ለማቋረጥ እንዳስፈለገ ገልፀዋል፡፡
የዳታ ሲስተሙን ለማዘመን የሚረዱ የማሻሻያ ስራዎችን እየተሰሩ መሆናቸውን ያነሱት አቶ ሙሉቀን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አገልግሎቱን በድጋሚ በተሻለ ፍጥነትና ጥራት ለማስጀመር ጥረት እንደሚደረግ ገለፀዋል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡



