ባሳለፍነው ሳምንት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደ ሀገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን የገቢ ኮንትሮባንድ 47 ሚሊዮን 535ሺ 362ብር፤ ወጪ ደግሞ 2 ሚሊዮን 953ሺ 432ብር፣ በድምሩ የ50 ሚሊዮን 488ሺ 794ብር ግምት እንዳላቸውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡
ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን 42 ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ታውቋል፡፡






