የጸረ ሙስና ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በ2013 በጀት አመት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጐች ሀብትና የገቢ ምንጮቻቸውን ማስመዝገባቸው ተገለፀ።
ሶስተኛው በሀገር አቀፍ የሙስና ቅኝት ጥናት እና የጸረ ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ የተዘጋጀው አወደ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል።
በአወደ ጥናቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ሽታየ ምናለ እንደገለጹት፤ ሙስና የህሊና ጠንቅ ነው። ከጦር መሳሪያ ዝውውር፣ ከአለም አቀፍ የወንጀሎች፣ ዘግናኝ ተግባራት፣ የሰዎች ዝውውር እንደ ጥላ የሚከተል የሰላም ጸር የሆነ ተግባር ነው ብለዋል።
አክለውም በሀገራችን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ጀርባ ሙስና ዋነኛ ችግር መሆኑ ምክትል አፈጉባኤዋ አስረድተዋል።
በሀገራችን ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያ ቀውሶችን ብቻ መመልከት የሙስናን አስከፊነት መገንዝብ ይቻላል ያሉት አፈጉባኤዋ፤ የህዳሴው ግድብም የዚሁ ጠንቅ ሰለባ እንደነበር አስታውሰዋል።
ለወንጀሎች መብዛትና ለሰዎች መፈናቀል ሙስና ከጀርባ እንዳለ ጠቁመው፤ ሙስና ያለበትን ጥልቀት ለማወቅ በብዛት የሚስተዋሉ የሙስና አይነቶችን ለመቅረፍ መለየትና ጥልቀት ያለው ጥናት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል
የፌዴራል የስነምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ወዶ ዋጦ እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ በሀገር ደረጃ የትውድል ግንባታና ሙስና የመከላከል ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የጸረ ሙስና ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በ2013 በጀት አመት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጐች ሀብትና የገቢ ምንጮቻቸውን ማስመዝገባቸውም በአወደ ጥናቱ ላይ ተገልጿል።
በተቋማት የብልሹ አሰራርን በመለየት የጸረ ሙስናን ትግል ማድረግ ያስፈልጋል መባሉን ከኢ.ፕ.ድ ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል።



