በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌት እና ስራ ላይ ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቧን እንደምትቀጥል  ሱዳን አስታወቀች

0
342

ሱዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ቢጠናቀቅም በግድቡ ሙሌትና አሰራር ላይ ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቧን እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ አስታውቀዋል ፡፡

ሃምዶክ የኢድ አል-አድሃ በዓልን አስመልክቶ ለህዝቡ ባስተላለፉት ንግግር የግድቡ ጉዳይ በመንግሥታቸው ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሆኖ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

“የኢትዮጵያ መንግስት የአንድ ወገን እርምጃዎችን በመቀጠል የሁለተኛውን ዙር የግድቡን ሙሌት ይፋ ማድረጉን ቢገልጽም ከአንድ ወገንተኝነት እንዲቆጠብ እና በዓለም አቀፍ ህግ አስገዳጅ ስምምነት መሰረት ሊሞላና ሊሰራ እንደሚገባ ጥሪያችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ማለታቸውን የሱዳን ትሪቡን ዘግቧል ፡፡

የሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ይህንን ግብ ለማሳካት አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ እናደርጋለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባል የሆኑት አቶ ይልማ ስለሺ በበኩላቸው ሁለተኛው ሙሌት ዝቅ ያለና የተፋሰስ አገሮችን የማይጎዳ መሆኑን አስታውቀው፤ ሦስቱን አገሮች የሚጠቅውን ይህን የግድብ ፕሮጀክት ለማሳካት ሱዳን እና ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ማክሰኞ እለት የሚታወስ ነው ማድረጋቸውከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ጋር በነበራቸው ቆይታ በመጋቢት ወር 2019 በሶስቱ ሀገራት በተፈረሙ መርሆዎች መሠረት በክረምት ወቅት ሁለተኛው ሙሌት መከናወኑን መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here