የአለም የምግብ ፕሮግራም ለፌደራል መንግስት ባቀረበው እና በተሰጠው ፍቃድ መሰረት በዛሬው እለት ኹለተኛ በረራውን ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ በመነሳት ወደ መቀሌ ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ይህ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የዛሬው በረራ መንግሰት በትግራይ ክልል የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀበት ጊዜ ወዲህ ኹለተኛው በረራ መሆኑ ተገልጿል።
በየሰብዓዊ ድጋፍ መስጫ ቁሳቁሶችን የያዘው አውሮፕላን ከ30 በላይ የሚሆኑ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን አብሮ ማሳፈሩም ታውቋል።



