የዓለም የምግብ ፕሮግራም ወደ መቐለ ከተማ 2ተኛውን በረራውን ሊያደርግ ነው

0
665

የአለም የምግብ ፕሮግራም ለፌደራል መንግስት ባቀረበው እና በተሰጠው ፍቃድ መሰረት በዛሬው እለት ኹለተኛ በረራውን ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ በመነሳት ወደ መቀሌ ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የዛሬው በረራ መንግሰት በትግራይ ክልል የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀበት ጊዜ ወዲህ ኹለተኛው በረራ መሆኑ ተገልጿል።

በየሰብዓዊ ድጋፍ መስጫ ቁሳቁሶችን የያዘው አውሮፕላን ከ30 በላይ የሚሆኑ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን አብሮ ማሳፈሩም ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here