የቀድሞው የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብረሃ ደስታ ከሀገር እንዳልወጣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከልክያለሁ ሲሉ ገለፁ።
አቶ አብረሃ ደስታ ዛሬ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው አዲስ አበባ እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን “ከዓመታት በፊት የታሰርኩበትና ነፃ የወጣሁበት ክስ እንደገና ተቀስቅሶ እንድከላከል ለሐምሌ 20, 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቶኛል።
ከሐምሌ 20 በሓላ ከጠፋሁ ያው ታስሬያለሁ ማለት ነው። ሳልታሰር ከቆየሁ መንገድ ሲከፈት ወደ ትግራይ እመለሳለሁ!” ሲሉ አስፍረዋል።
“እንደገና ተቀስቅሷል” ስላሉት ክስ ምንነት አቶ አብርሃ ያሉት ነገር የለም።



