የደቡብ ክልል ተጨማሪ የልዩ ሀይል አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ለማሰማራት የሽኝት መርሐ ግብር በሀዋሳ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ።
የህወሓት ቡድን በሀገሪቱ እያካሄደ ያለውን የሽብር ተግባር ለመከላከል የደቡብ ክልል ከዚህ ቀደም የልዩ ሀይል አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ማሰማራቱ ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ ክልሉ ለሁለተኛ ዙር የልዩ ሀይል አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ለማሰማራት በሀዋሳ የሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በሽኝት መርሐ ግብሩም የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት ከ300 የሚበልጡ የልዩ ሀይል አባላት ሀገራዊ ግዳጃቸውን በመወጣት ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።





