ከ18 ዓመት በላይ ሆነው ተጓዳኝ ሕመም ላለባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት ተጀመረ

0
1225
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ሆነው ተጓዳኝ ሕመም ላለባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ቀደም ሲል ክትባቱን ያላገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለመከተብ፤ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ትግበራ መገባቱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

በመዲናዋ ሁሉም ጤና ጣቢዎች ክትባቱ መሰራጨቱንና ዕድሜው ከ35 ዓመት በላይ የሆነ፤ እንዲሁም ከ18 ዓመት በላይ ሆኖ ተጓዳኝ ሕመም ያለበት ማንኛውም ሰው መከተብ እንደሚችል አስታውቀዋል።

በሥራ ባህሪያቸው ተጋላጭ መሆናቸው የተለዩ የ105 የመንግሥትና የግል ተቋማት ሠራተኞች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ዮሐንስ እንደገለፁት ከሆነ ክትባቱ በሁሉም ጤና ጣቢዎች በነጻ የሚሰጥ ሲሆን፤ ክፍያ የሚጠይቅ አካል ካለ ኅብረተሰቡ ጥቆማ መስጠት አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here