የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13 ድረስ መራዘሙ ተገለፀ

0
626

ሐሙስ ጥር 5 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ከታህሳስ 26/2014 – ጥር 6/2014 ድረስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

እስካሁን ዕጩ ኮሚሽነሮችን ለመጠቆም ዜጎች ያሳዩት ተነሳሽነትና እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ የሚያበረታታ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል፡፡

ይሁንና ኮሚሽኑ ከሚኖረው ከፍተኛ አገራዊ ኃላፊነት አንፃር ተጨማሪ ዕጩዎችን ህዝቡ እንዲጠቁም እንዲሁም የአገሪቱን ብዝሃነት ታሳቢ በማድረግና በተለያዩ ምክንያቶች መጠቆም ላልቻሉ ዜጎች ዕድሉን ለመስጠት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13/2014 ድረስ የተራዘመ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት አስታውቋል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here