ሰበር ዜና – የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ሰለሞን ታደስ በጥይት ተመተው ተገደሉ

Views: 482

 

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ሰለሞን ታደስ ዛሬ የካቲት 13/2012 በቡራዩ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ።

ከኮሚሽነር ሰለሞን ጋር አብረው የነበሩት የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የልዩ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተስፋዬ ድንቁም በጥይት ተመተው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸውመሆኑን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ሁለቱ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ላይ ጥቃቱን የሰነዘረው አካል ማንነት እስካሁን ግልጽ አለመሆኑን እና እስካሁን በወንጀሉ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው አለመኖሩንም የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ  ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ጌታቸው እንዳሉት በሁለቱ ባለስልጣናት ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው የቡራዩ ከተማ አስተዳደር አቅራቢያ ምሳ እየተመገቡ ሳሉ ነበር።

በጥይት ተመተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙት ኮማንደር ተስፋዬ የሚገኙበትን ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም።

ፎቶ ከኢቢሲ

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com