በአጣዬ በአሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሓት የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

0
560

የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በአጣዬ ከተማ በአሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሓት የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ።
በከተማዋ ህወሓትና ሸኔ በጋራ ሆነው 420 መኖሪያ ቤቶችና 50 ግሮሰሪና ሆቴሎችን አውድመዋል። ከ250 በላይ ሰዎችንም መግደላቸውን የከተማዋ አስተዳድር ከንቲባ ጽኅፈት ቤት አሳውቋል።

ከተማዋን መልሶ ለመገንባትም እስካሁን በተሠራ ሥራ የ45 ቤቶች ግንባታ በይፋት ልማት ማኅበርና በመንግሥት መጀመሩ፣ ቀሪ ቤቶችን ለመገንባት ሥራዎች ተጀምረዋል ሲል የከተማዋ ከንቲባ ጽኅፈት ቤት ገልጿል።
የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ በአማራ ልማት ማኅበር አስተባባሪነት 160 ሺሕ ዶላር በሆነ ወጪ በመጀመሪያ ዙር ዘጠኝ ቤቶችን ለመሥራት ተረክቧል ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በበኩሉ፣ የፈረሱ ቤቶችን የመገንባት ሥራው ይቀጥላል፤ ተጨማሪ ቤቶችን ለመገንባትም ዕቅድ ተይዟል ሲል አሳውቋል።
የአማራ ልማት ማኅበር እንዲሁ፣ ዳያስፖራው የደረሠውን ጉዳት ለሌሎች በማሳወቅ ከተሞችን መልሶ ለመገንባት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡ ተመላክቷል።


ቅጽ 4 ቁጥር 167 ጥር 7 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here