10ቱ ከኢትዮጵያ ብዙ ምርት የወሰዱ የአውሮፓ አገራት

Views: 369

ምንጭ፡ – ብሔራዊ ባንክ (2018/19)

ባለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ወደ 677 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምርት ወደ አውሮፓ አገራት ልካለች። ይህ የአገሪቷን አጠቃላይ የውጭ ንግድ አንድ አራተኛ ይስተካከላል። ይህ ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ አገራት የምትልከው ምርት ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ከሚላከው የላቀ ሲሆን፣ ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ በ143 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ያለ ነበር።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ2018/19 ባወጣው ዘገባ መሠረት የኢትዮጵያ ምርቶችን በመግዛት በቀዳሚነት የሰፈረችው ኔዘርላንድ ስትሆን 210.5 ሚሊዮን ዶላር ከኔዘርላንድ የተገኘ ነው። ጀርመን እና ቤልጂየም ከኔዘርላንድ በእጥፍ እና ከዛመ በላይ ባነሰ የገንዘብ መጠን ከኢትዮጵያ በሚገዙት ምርት ተከታትለው ተቀምጠዋል። ከእነዚህ የአውሮፓ አገራት በመቀጠልም ጣልያን እና ዩናይትድ ኪንግደም ይከተላሉ። በዝርዝሩ ከኢትዮጵያ ምርት በመግዛት ትንሹን ወጪ ታወጣለች ተብሎ የተመዘገበችው ሩስያ ናት። ይህም 12.1 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ 3.3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምርት ከአውሮፓ አገራት ያስገባች ሲሆን፣ ይህም ከአገሪቷ አጠቃላይ የውጭ ንግድ ገቢ በ700 ሚሊዮን ዶላር የላቀ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 68 የካቲት 14 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com