በአብየ የተሠማራው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል ሊተካ ነው

0
404

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሠላም ማስከበር ዘመቻ ኃላፊ ጅን ፔሬ ላክሮክስ እንደገለጹት፣ በአብየ ሚገኘውን የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል የመተካቱ ሒደት በቀጣይ ወር ይጀምራል ተብሏል።
ሱዳን በአብየ ያለው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ጥያቄ አቅርባ የነበረ ሲሆን፣ ጥያቄዋም በተመድ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል። ሱዳን የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ጦር ይወጣ ያለችው በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል በድንበር ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው።

ኃላፊዋ ላክሮክስ ይህን ያሉት ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ባደረጉት የስልክ ወይይት ነው ተብሏል። የሽግግር ምክር ቤቱ እንደገለጸው አልቡርሃን ከተመድ ኃላፊ ጋር ያደረጉት ውይይት የተመድ ‹ኢንትሪም ሴኩሪቲ ፎርስ ፎረ አብየ› ውስጥ ያሉት የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ወታደሮችን በሱዳን መንግሥት በተጠየቀው መሠረት ለመተካት የመከረ ነበር።
በስልክ ወይይቱ ወቅት ላክሮክስ የመተካቱ ሥራ በፈረንጆቹ ቀጣይ የካቲት ወር እንደሚጀመርና እስከ ፈረንጆቹ መጋቢት 2022 እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸው ተዘግቧል።


ቅጽ 4 ቁጥር 168 ጥር 14 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here