በአማራ ብሔራዊ ክልል በሚገኙ ኹለት ጥብቅ ሥፍራዎች ብቻ ህወሓት በከፈተው ወረራ ሳቢያ ከ367 ሚሊዮን ብር በላይ የሀብት ውድመት መድረሱን የክልሉ አካባቢና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።
በዚህም የሀብት ውድመቱ የደረሰው የበርካታ ዱር እስንስሳት እና ብዝኃ ሕይዎት መገኛ በሆኑት የመንዝ ጓሳ ማህበረሰብ አቀፍ ጥብቅ ሥፍራ እና በአቡነ ዮሴፍ ዚጊቲና አቡሃይ ጋራ ማህበረሰብ ጥብቅ ሥፍራ ናቸው ተብሏል።
በመንዝ ጓሳ ምህበረሰብ አቀፍ ጥብቅ ስፍራ አጠቃሊይ የደረሰዉ ቁሳዊ ጉዲት በገንዘብ ሲተመን 206 ሚሊዮን 231 ሺሕ 805 ብር የሚገመት መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል። በዚህ ጥብቅ ሥፍራ ከማህበረሰብ ልጅው የወደመዉና የተዘረፈዉ ንብረት 181 ሲሆን፣ 1 ሚሊዮን 68 ሺሕ 305 ብር ይገመታሌ።
በተኩስ ሌዉዉጡ ለአጨዲ ደርሶ የነበረ 3198 ሄክታር ጓሳ በአብሪ ጥይት መቃጠሉን እና ይህም የጓሳዉ 80 በመቶ ሲሆን፣ 428 ሺሕ 921 ሸክም ወይም 204 ሚሊዮን 46 ሺሕ 400 ብር ያወጣ እንደነበር ነው ባለስልጣኑ ለአዲስ ማለዳ በላከው መረጃ ያመላከተው።
እንደ ቀይ ቀበሮ፤ ጭሊዳና ድኩላ ያሉ የዱር እንስሳት ወደ ሰዎች መኖሪያ kመሰደዳቸውም በላይ፣ 27 ሰሳ ፤ 10 ድኩላ እንዲሁም 7 ሚዲቋዎች የታደኑ እና የተቃጠሉ መሆናቸውንም ጨምሮ አስገንዝቧል።
በዚሁ ጥብቅ ሥፍራ ውስጥ ይገኙ የነበሩ እና የማሀበረሰቡ ንብረት የሆኑ ዘመናዊ ሎጅዎችና የሰራተኛ መኖሪያ ቤቶችም መውደማቸው ተመላክቷል።
የህወሓት ወራሪ ቡድኑ በክልሉ በከፈተው ጦርነት ምክንያት ሌላኛው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የተገለጸው አቡነ ዮሴፍ ዚጊቲና አቡሃይ ጋራ ማህበረሰብ ጥብቅ ሥፍራም እንዲሁ፣ በአጠቃሊይ 161 ሚሉየን ብር የሚገመት፣ በቢሮ፤ በሎጅ፤ በደንና ጓሳ ቁሳዊ ጉዳት መድረሱ ነው የተገለጸው።
በዚህም 1 ሚሊዮን 712 ሺህ 100 ብር የሚገመት የቢሮና የመሰክ መገልገያዎች የተዘረፉና የወደሙ መሆናቸው ተመላክቷል።
እንዲሁም 6 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ 4 የማህብረሰቡ ሎጅ ቤቶች ሙሉ በሙለ ወድመዋል ነው የተባለው።
የአቡሃይ ጋራ ሙሉ የጦር አውድማ ሆኖ ስለነበር፣ 982 ሺህ ብር የሚያወጣ የጎብኝዎች ማስተናገጃና ማረፊያ ቁሳቁስ ሙለ በሙለ ተዘርፏል፣ 3000 ሄክታር 150 ሚሊየን ብር የሚገመት የጓሳ ሳርና ደን መጨፍጨፉም ተነግሯል።
በቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክም እንዲሁ በንብረትና ተቋማት ላይ የደረሰ የከፋ ጉዳት ባይኖርም፣ በቀጥታ ጉዳቱ በጋምቦና ተንታ ወረዳ የፓርኩ አካሌ ላይ ቢሆንም በሁለም ደንና የዱር እንስሳት ላይ ጉዲት መድረሱ ታውቋል።
ህብረተሰቡ ወደ ፓርኩ ክልል የቤት እንስሳትን ይዞ ከመግባቱም ሌላ፣ ፓርኩ ሽፍቶችን ይደብቃሌ በሚል ደን መመንጠር እና ሳር በማጨድ ጉዳት እንደደረሰበትም ተመላክቷል።
በተጨማሪም በሁለም አካባቢዎች በርካታ ዛፎችን በመቁረጥና በመመንጠር እንዲሁም፣ በፓርኩ ውስጥ በሚያቋርጠዉ መንገድ የሚጓዙ ታጣቂዎች ጥይት በመተኮስ የዱር እንስሳትን መረበሽና መግደላቸውም ነው የተገለጸው።
በሌሎች በጥብቅ ሥፍራዎችም እንዲሁ ጉዳት ያጋጠመ ሲሆን ለአብነተም፣ በጉና ማህበረሰብ ጥብቅ ሥፍራና ባኩሳ ብሄራዊ ፓርክ ህገወጥ የህግ ማሰከበርና መደበኛ ስራዎች ባለፉት 4 ወራት ባለመከናወናቸዉ ልቅ ግጦሽ፣ ደን ምንጠራና ሳር አጨዳ መበራከቱን ለማወቅ ተችሏል።
ጥብቅ ሥፍራዎችን አቋርጠዉ የሚንቀሳሰቀሱ የህግ አስከባራ የጸጥታ ሃይሎችም በሚዘዋወሩበት ጊዜ ጥይት በመተኮስ የዱር እንስሳትን የማደን፣ የማሰበርገግ እና መሰል ህገወጥ ተግባራት መበራከታቸውን ባለስልጣኑ አሳውቋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ የዱር እንስሳት በጦርነት ተጎጂና ተቆጭ በመሆናቸውም፣ በላጋምቦና በላሊበላ አካባቢዎች ከ40 በላይ የወራሪ ቡድኑ አባላት በዱር እንስሳት መገደላቸው ነው የተመላከተው።
በመጨረሻም የወደሙና ጉዳት የደረሰባቸው እነዚህ ሥፍራዎችን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ፣ ለመንዝ ጓሳ ጥብቅ ሥፍራ 5 ሚሉዮን ብር፣ ለአቡነ ዮሴፍ 11 ሚሉየን ብርና የተሸከርካሪ ድጋፍ ያስፈልጋል ሲል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለአዲስ ማለዳ በላከው መረጃ አትቷል።
ተመሳሳይ ርዕስ
ጦርነቱ በግብርናው ዘርፍ ላይ ያስከተለው ጉዳት – ዜና ከምንጩ (addismaleda.com)
በአማራ ክልል በደባርቅ ከተጠለሉት በስተቀር በጦርነቱ ሳቢያ ተፈናቅለው የነበሩ ኹሉም ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸው ተገለጸ – Addis Maleda
በአማራ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ አባወራዎች የጤና መድኅን ክፍያ የመክፈል አቅም የላቸውም ተባለ – Addis Maleda
ቅጽ 4 ቁጥር 168 ጥር 14 2014



