የዙምባቤዌ ቢሊየነር ከኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ ነው

Views: 133

በዙምባብዌው ቢሊየነር ስትራይቭ ማሲያዋ ባለቤትነት የሚተዳደረው ኢኮኔት ግሎባል የተባለው ኩባንያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ከኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ለማግኝት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ብሉምበርግ ዘገበ፡፡

የኩባንያው ቃል አቀባይ ለብሉምበርግ በሰጡት ምላሽ ኩባንያው በሥሩ ባቀፋቸው ድርጅቶች በኩል ኢትዮጵያ ላይ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስቸውለውን ፈቃድ ለማግኘት እንቀስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢኮኔት በዙምባብዌ፣ በሌሴቶ፣ በብሩንዲ የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በተለያዩ የአውሮፓ እና የደቡብ አሜሪካ አገራት ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ውስጥም ተሰማርቶ ይገኛል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com