ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ ለቻይና ህዝብና መንግስት ለአገሪቱ አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አዲስ ዓመቷን እያከበረች ለምትገኘው ቻይና እና ሕዝቦቿ አዲሱ ዓመት የደስታ እና ብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
አክለውም የቻይና መንግስት ኢትዮጵያ በገጠማት አስቸጋሪ ወቅት ላይ ላደረገው ድጋፍ እና አጋርነትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




