“ሰራዊታችን ውስጣዊ አንድነቱን መጠበቅ አለበት” ጀነራል ባጫ ደበሌ

0
980

ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሥራዎች አስተባባሪ ጀነራል ባጫ ደበሌ ሰራዊታችን ውስጣዊ አንድነቱን መጠበቅ አለበት ሲሉ አሳሰቡ፡፡

የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ሰራዊታችንን በዘርና በኃይማኖት ለመከፋፈል በሚዲያ የሚያሰራጩትን አሉባልታዎች በመስማት የውስጣችንን አንድነት መሸርሸር የለብንም ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ማንኛውም ሰራዊት በመካከላችን ከተቀላቀለ ፕሮፌሽናል የኢትዮጵያ ሰራዊት ነው፣ የእኛ አላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማሰከበርና ሰላሟን ማስጠበቅ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የመሃንዲስ ሥራ እንደ ሥሙ ምንጊዜም ከባድ ነው፣ መሃንዲስ የለሌው ሰራዊት መሪ እንደሌለው አይነ ስውር ነው፣ ዛሬ ያገኛችሁት የሜዳሊያና ሌሎች ሽልማቶች የግዳጃችሁ አፈፃፀም ውጤት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌ/ጀነራል ደስታ አብቼ፣ አገራችን አትበተንም በማለት የመሃንዲስ ክፍሉ ከፍተኛ አስተዋፆኦ አደርጓል ብለዋል፡፡

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በግዳጅ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷቸዋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here