አርብ ጥር 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ላይ የሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጓል።
የምክር ቤቱ መረጃ እንዳመለከተው በተለያዩ አግባቦች በተጠቆሙት 42 የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከዛሬ ጀምሮ የሕዝብ አስተያየት ይሰጥባቸዋል።
በዚሁ መሠረት ይህንን ማስፈንጠሪያ http://www.hopr.gov.et/am/web/guest/dialog-candidate በመጫን አስተያየት መስጠት እንደሚቻል ምክር ቤቱ አስታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




