ማክሰኞ የካቲት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የቄለም ወለጋ ቅርንጫፍ ንብረት የሆኑና ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው ኹለት የታርጋ ቁጥር ET05-02121 እና ታርጋ ቁጥር ET05-02108 አምቡላንሶች ሰሞኑን በቄለም ወለጋ ለሰብዓዊ አገልግሎት ሲንቀሳቀሱ በውል በማናውቀው ሁኔታና በግዳጅ ተወስደውብናል ሲል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስታወቀ፡፡
ድርጊቱ ኢትዮጵያ የፈረመችውን አለምአቀፍ የጄኔቫ ኮንቬንሽን የሚፃረርና፣ ከማህበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑንም ማህበሩ ገልጿል።
ስለሆነም ከላይ የታርጋ ቁጥራቸው የተገለፁት ኹለት አምቡላንሶች በማኅበሩ ቁጥጥር ሥር የሌሉ መሆኑን ተረድተው ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ! አምቡላንሶቹን ወደ ማህበሩ ተመልሠው ለህብረተሠቡ የተለመደውን ሰብዓዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲሰጠን ሲል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በማህበሩ እና በተገልጋይ ወገኖች ሥም ጠይቋል፡፡
——————————
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



