ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር ከአልኮል ነፃ ነው የተባለና ‹‹ንጉሥ›› የተሰኘ የማልት (ብቅል) መጠጥ አምርቶ ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ።
ንጉሥ የተሰኘው መጠጥ ከአልኮል ነፃ በመሆኑ ከለስላሳ መጠጦች ጋር እንደአማራጭ መቅረብ እንዲችል ሆኖ መዘጋጀቱን አክሲዮን ማኅበሩ አስታውቋል።
አምራች ድርጅቱ በላከው መግለጫ የአዲሱ ምርት አቅርቦት በመጀመሪያ በአዲስ አበባ እና ደብረ ብርሃን እንደሚሆን አመልክቷል።
‹‹ንጉሥ›› በማኅበረሱ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እና ስያሜውን ለማስታወስም ቀላል ሆኖ በመገኘቱ ለምርቱ መጠሪያ እንዲሆን መመረጡን ገልጿል።
የአክሲዮን ማኅበሩ መጀመሪያ ስምንት ሺህ በሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ባለአክስዮኖች የተቋቋመ ሲሆን ሽያጩንም በ2ዐዐ8 መጀመሩ ይታወሳል። የቢራ መጥመቂያ ፋብሪካውንም ደብረ ብርሃን ላይ ገንብቶ ወደ ሥራ ከገባ ዓመታት ተቆጥረዋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 14 የካቲት 9 ቀን 2011