ሕዝቡ ለመከላከያ ሠራዊት ክብር እንዲሰጥ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠየቁ

0
1053

መተኪያ የሌላትን ሕይወት ለመሰዋት በመዘጋጀት ጭምር የአገር አለኝታ የሆነው የመከላከያ ሠራዊት ለጠላቶች የፍርሃት፣ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ የኩራት ምንጭ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሠራዊቱ የሚገባውን ክብር እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

ሠራዊቱ እንደ ተቋም ያሉበትን ክፍተቶች እያረመ የሚሔድ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ በሕዝብ መገልገያ ቦታዎች ሕዝቡ ቅድሚያ በመስጠት ለሠራዊቱ ያለውን ክብር እንዲያሳይ ጠይቀዋል።

የአገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን በበኩላቸው ሠራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ ያለማመንታት ለመፈፀም እየተጋ ስለመሆኑ አንስተው ሕይወቱን እስከመስጠት የሚደርስ ነው ብለዋል። አያይዘውም ሕይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉ አባላት ክብር እንዳላቸውና ቤተሰቦቻቸውም የእነዚህ ጀግኖች ቤተሰቦች በመሆናቸው ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

7ኛው የአገር መከላከያ ሠራዊት ቀን በአዳማ ሲከበር የተገኙት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ማዕበል በተቀሰቀሰበት ወቅት በሠራዊቱ ስም የተፈጸሙ ግድፈቶች በእኩይ አመራሮች የተደረጉ እንጂ ሠራዊቱን በጅምላ የሚወክል እንዳልሆነ አስገንዝበዋል። ‹‹ሠራዊቱ የሉአላዊ ክብራችን ዋልታ ነው›› ያሉት ለማ ለእድገቱ ማገዝ እንደሚገባም አክለዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 14 የካቲት 9 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here