ዓለም ባንክ ለሶማሌ ክልል 64 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መደበ

0
735

አርብ የካቲት 11 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ዓለም ባንክ በሶማሌ ክልል ለተከሰተው ድርቅ አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ 64 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ።

ከተመደበው ድጋፍ ውስጥ 38 ሚሊዮን ዶላሩ አሁን የሚሰጥ መሆኑን ሙስጠፌ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

የዓለም ባንክ በዚህ ወሳኝ ጊዜ ድጋፉን በማድረጉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን የተመራ ልዑክ በዛሬው ዕለት ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ መግባታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here