ምንጭ፤ ዋን ስቴፕ ፎር ዋርድ (2021)
በዓለማችን ያሉ ሰዎች በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ቦታዎችን ለመጎብኘት ከአንዱ ወደ ሌላኛው አገር ሲተሙ ይስተዋላሉ። ለጉዟቸው ዋነኛ ምክንያትም በሚኖሩበት አካባቢ የሌሉና በሌላ ቦታ ያሉ ማራኪ ቦታዎችን ለማወቅ፤ ለመዝናናትና ለመሳሰሉት ዓላማ ነው።
ዋን ስቴፕ ፎር ዋርድ የተሰኘው ድረ ገጽ በ2021 ያጠናቀረው ዳሰሳ እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ከላይ የተዘረዘሩት 10 በየዓመቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጎብኝዎች የሚተሙባቸው አገራት ናቸው።
ዳሰሳው እንደሚያመላክተው ከዓለም አገራት መካከል ከፍተኛ ጎብኝዎች ያላት አገር ፈረንሳይ ስትሆን፤ 82.6 ሚሊየን ጎብኝዎች እንዳሏት ነው ማወቅ የተቻለው።
ከፈረንሳይ በመቀጠልም ዩናይትድ ስቴትስና ስፔን የኹለተኛውንና የሦስተኛውን ደረጃ የያዙ ሲሆን፤ 30 ሚሊዮን ጎብኝዎች ያላት ቱርክ በአስረኛ ደረጃ ትገኛለች።
ቅጽ 4 ቁጥር 172 የካቲት 12 2014



