ከ1400 በላይ የኤርትራ ስደተኞች ወደ “አለምዋጭ” ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ተዛወሩ

0
415

ዕረቡ የካቲት 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከ1400 በላይ የኤርትራ ስደተኞች በሰሜን ጎንደር ዞን ወደ ተገነባላቸው “አለምዋጭ” ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ መዘዋወራቸውን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ።

ስደተኞቹ ከሰኔ 21/2013 ጀምሮ በዳባት ወረዳ በሚገኙ በሶስት የህዝብ ተቋማት ውስጥ ተጠልለው የቆዩ እንደነበሩም አገልግሎቱ ገልጿል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሰሜን ጎንደር ዞን እና የዳባት ከተማ አስተዳዳሪዎች፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ተወካዮችና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here