ሴታዊት ለሴት ፖለቲከኞች ያዘጋጀችው የውይይት መድረክ ተሰረዘ

Views: 154

ሴታዊት ንቀናቄ በዘንድሮው 2012 ለሚደረገው አገራዊ አቀፍ ምርጫ ላይ ሴቶች ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዳሜ መጋቢት 12/2012 ለማድረግ ያዘጋጀቸው የውይይት መድረክ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተሰረዘ።

አብዛኛው ሴቶች በፖለቲካው ዘርፍ  በግልም ይሁን በፓርቲ ውስጥ ሲሳተፉ አንመለክትም ያሉት የሴታዊት የኮምዩኒኬሽን ባለሙያ ከአምላክነሽ ያሲን፣ ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ወቅት እንዲሁም ከምርጫው በኋላ ሴት ተወዳዳሪዎች ኃላፊነታቸውን እንዴት እንደሚወጡ እና ስለሚገጥማቸው ተግዳሮቶች መፍትሔ ለመስጠት የሚመክር ውይይት ይሆናል ተጠብቆ ነበር።

በቀጣይም ሴታዊት የውይይቱን ቀን ይፋ እንደምታደርግ ለአዲስ ማለዳ አስታውቃለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከመጋቢት 07/2012 ጀምሮ ትምህርት ቤቶች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት እንደሚዘጉ መወሰናቸውም ይታወሳል።

 

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com