በሸማቾች በኩል ያለው የዘይት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑ ተገለፀ

0
824

ማክሰኞ የካቲት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ቀደም ብሎ የገባው የዘይት ምርት በየመሸጫ ሱቆች ውስጥ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረጉን ሃላፊነት እየተወጣው መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የህብረት ሥራ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ደብሪቱ ላለም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ ትክክለኛ ምክንያቱ ባልታወቀ መልኩ የተከሰተው የዘይት ዋጋ መናር በሸማች ማህበራቱ በኩል ቀደም ብሎ በገባው የዘይት መሸጫ ዋጋ ላይ ምንም አይነት ለውጥን አለማሳየቱን እና የአቅርቦት እጥረቱ ግን ቀደም ብሎም መኖሩን ተናግረዋል፡፡

አሁንም ምርቱ በሚገኝባቸው መሸጫ ሱቆች ዋጋው ምንም አይነት ለውጥ እንዳልተደረገበትም አስታውቀዋል።

ባለፉት ቀናት አምስት ሊትር ዘይት በሸማች ማህበረቱ በኩል በሚቀርበው የእሁድ ገበያ አማካኝነት ከ 650 እስከ 700 ብር ድርስ ሲሸጥ ነበር ሲሉም ገልፀዋል፡፡

የኢንዱስትሪ፤ የግብርና እንዲሁም የባልትና ውጤቶች በ10 ዩኒየኖች አማካኝት ለ 148 ሸማች ሥራ ማህበራት ተደራሽ የሚደርጉ ሲሆን እነዚህ ሸማች ማህበራትም በየወረዳው በአማካኝነት ከ7 እስከ 3 ያክል ሱቆች እንዳላቸው ደብሪቱ ተናግረዋል፡፡

ሌሎች የግብርና ምርቶችን በተመለከተ በአነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የከተማው ህብረት ሥራ ኤጀንሲ እየሰራ መሆኑንም መናገራቸውን የራዲዮ ጣቢያው ዘግቧል፡፡

ይሁንና በአሁኑ ሰዓት የተከሰተውን የዘይት ዋጋ መናር ለመቆጣጠር ባለድርሻ አካላት ትኩረት አድርገው መስራት አላባቸው የሚሉት ደብሪቱ፤ ህብረተሰቡንም ከዚህ ቀውስ መታደግ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here