በህወሃት ዳግም ጥቃት የተነሳ የተፈናቀሉ ኤርትራውያን ስደተኞች የመጠለያ ካምፕ ቀየሩ

0
523

ማክሰኞ የካቲት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን ዳግም በከፈተው ጥቃት የተነሳ የተፈናቀሉ ኤርትራውያን ሥደተኞች የመጠለያ ካምፕ መቀየራቸውን የሥደተኞች እና የሥደት ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ።

የሥደተኞች እና የሥደት ተመላሾች አገልግሎት ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ፤ ቡድኑ በፈፀመው አዲስ ጥቃት በአፋር ክልል ከሚገኘው በርሃሌ ጣቢያ የተፈናቀሉ ኤርትራውያን ሥደተኞች ወደ ሰርዶ የመጠለያ ካምፕ መዛወራቸውን አስታውቋል፡፡

በአፋር በርሃሌ የስደተኞች ጣቢያ የቆዩት ኤርትራውያን ስደተኞች ከህወሃት ጥቃት ለመሸሽ በትናንትናው ዕለት አዲስ ወደ ተቋቋመው ሰርዶ የሥደተኞች ማቆያ ካምፕ ተጓጉዘው መድረስ መጀመራቸውም ነው አገልግሎቱ ገለፀው።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here