ምንጭ፡- ስታቲስታ 2021/22
የሩስያ እና ዩክሬንን ጦርነት ተከትሎ ዓለም ጦሱ እንደሚተርፋትና እንደማይቀርላት ያጣችው አይመስልም። ይህም በአዳጊ አገራት እንደሚከፋ ከወዲሁ ብዙዎች ሥጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ይልቁንም የስንዴ ዕጥረት መከሰቱ አይቀሬ ነው ተብሏል። የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ የዓለም አገራትን ድጋፍ የሚፈልጉ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራ ይህ በእጅጉ አሳሳቢ ዜና መሆኑ እሙን ነው።
‹ስታቲስታ› የተባለውን ድረ-ገጽ ስንቃኝ፣ በዓለማችን ከፍተኛ የስንዴ አምራች የሆኑ አገራት ዝርዝርን አግኝተናል። በእርግጥም ያሠጋል። ምንም እንኳ በዝርዝሩ ቻይና እና ሕንድ ቀዳሚና ኹለተኛ ሆነው የተመዘገቡ ቢሆንም፣ ሩስያ እና ዩክሬንም በዓለም የስንዴ ገበያ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተሳትፎና ድርሻ አላቸው።
ቅጽ 4 ቁጥር 176 መጋቢት 10 2014



