የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 90 በመቶ መድረሱ ተገለፀ

0
1509

ሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የግንባታ ሥራው መስከረም 20 ቀን 2012 የተጀመረውና በዓይነቱ ልዩ ነው የተባለለት የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ግንባታ አሁን ላይ 90 በመቶ መፀናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በከተማዋ የመንገድ ግንባታ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የዋሻ ውስጥ መተላለፊያ መስመር ጨምሮ ተሻገጋጋሪ ድልድይ እና የፈጣን አውቶብስ መመላለሻ ኮሪዶርን አካቶ እየተገነባ የሚገኘው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ30-45 ሜትር የሚሆን የጎን ስፋት አለው።

ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው ዋና መንገድ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፤ አሁን ላይ ከቄራ እና ከቂርቆስ ወደ ጎፋ ማዞሪያ በሚወስዱት መንገዶች መጋጠሚያ ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ፣ የማሳለጫ ድልድዩ መቃረቢያ መንገዶች የሙሌት እና የሰብ ቤዝ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here