የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ፈተና ሂደት የሚያጣራ ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩን አስታወቀ

0
1556

ሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች የውጤት ችግር መግጠሙን ተከትሎ የተፈጠረውን ከፍተኛ ቅሬታ የሚያጣራ ቡድን ወደ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት ኤጀንሲ መላኩን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የተማሪዎች ውጤት ያሳሰበው የክልሉ ትምህርት ቢሮም ችግሩን ለመፍታት በርካታ ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱንገልጿል፡፡

በአሁን ሰዓትም ከክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮቸና ባለሙያዎች፣ከአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፣ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና መምህራን የተውጣጣ ቡድን ወደ ኤጀንሲው መላኩን አስታውቋል፡፡
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here