በነገው ዕለት በመላው አዲስ አበባ የህዝብ ውይይት እንደሚደረግ ተገለፀ

0
908

ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በነገው ዕለት ረቡዕ መጋቢት 14 ቀን 2014 በመላው አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎች፣ ክ/ከተሞች እንዲሁም በከተማ ደረጃ የህዝብ ውይይቶች እንደሚካሄዱ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

“በውይይቱ በየደረጃው ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎችና ሃሳቦች ይደመጣሉ” ያለው የከተማ አስተዳደሩ፤ የሚነሱት ጥያቄና ሀሳቦችም ለቀጣይ ሥራዎች ግብዓት ይሆናሉ ብሏል፡፡

በተጨማሪም የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ መጠናቀቅን ተከትሎ፤ የጉባኤውን ውሳኔዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ከህዝቡ ጋር የጋራ በማድረግ ቀጣይ ሥራዎች ላይ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎም እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here