በአፈር መደርመስ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

0
700

ዕረቡ መጋቢት 14 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በአፈር መደርመስ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በወረዳው ቀበና ኪዳነ ምህረት አካባቢ ለህንፃ ግንባታ መሰረት በቁፋሮ ላይ እያሉ የተቆፈረው አፈር በሰዎች ላይ ተደርምሶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፤ የኮሚሽኑ ፈልጎ ማዳን ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ አንድ ሰው ማትረፍ መቻሉንና ወደ ህክምና ማዕከል መወሰዱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በከተማዋ ለህንፃ ግንባታ የሚቆፈሩ መሬቶች መደርመስ አልፎ አልፎ የሚከሰት ቢሆንም፤ መጪው ጊዜ ክረምት በመሆኑ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የግንባታ ባለሙያዎች እና የሚመለከተው አካል ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይገባል ሲልም ኮሚሽኑ አሳስቧል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here