“ለመንግስት ያስገባሁት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፣ በጤና እክል ምክንያት ቀደም ብዬ ጡረታ ወጥቻለሁ፣”:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገ/ማርያም

0
1273

ዕረቡ መጋቢት 14 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ለመንግስት ያስገባሁት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፣ በጤና እክል ምክንያት ቀደም ብዬ ጡረታ ወጥቻለሁ ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገ/ማርያም ገለፁ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከ37 ዓመት በላይ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ያገለገሉት ተወልደ ገ/ማርያም በጤና እክል ምክንያት ቀደም ብለው ጡረታ መውጣታቸውን ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ ድረገፅ አረጋግጠዋል። አክለውም ለመንግስት ያስገቡት የመልቀቂያ ጥያቄም ተቀባይነት ማግኘቱን አሳውቀዋል።

ተወልደ ላለፉት 11 ዓመታት በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ያገለገሉ ሲሆን፤ ከዛ በፊት በካርጎ ክፍል ሀላፊነት፣ በአሜሪካ ኤሪያ ማናጀር በመሆን ወዘተ ሰርተዋል። በዚህም ወቅት “የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ሥራ አስፈፃሚ” የሚሉ ሽልማቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሽልማቶችን ለግላቸውም፣ ለአየር መንገዱም አስገኝተዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here