ዕረቡ መጋቢት 14 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት፤ የቀድሞ ጠ/ሚ ሀይለማርያ ደሳለኝ እና የቀድሞ የጀርመን አንባሳደር ፍስሀ አስገዶም ጨምሮ ሌሎችንም ምስክሮች በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ የመከላከያ ምስክርነታቸው ለመስማት ከግንቦት 3 እስከ ግንቦት 5 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ችሎቱ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት መሟላቱን በተመለከተ ከፍርድ ቤቱ አስተዳደር ጋር ተነጋግሮ ምስክር የሚሰማበትን ጊዜ ለማሳወቅ ለዛሬ መቅጠሩ ይታወቃል።
የቀድሞ የኢፊዴሪ ብረታብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ( ሜቴክ) ዋና ዳሪክተር የነበሩት ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው በተከሰሱበት የዕርሻ መሳሪያ ግዢ ሙስና ክስ ላይ በመከላከያ ምስክርነታቸው የተዘረዘሩት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ የቀድሞ የጀርመን አንባሳደር በአሁን ወቅት በአሜሪካ የሚገኙት ፍስሀ አስገዶም፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ካውንስለር ካሳ እና የቀድሞ የፖላንድ አንባሳደር ጭምር ባሉበት ቦታ ሆነው በበየነ መረብ ምስክርነታቸው እንዲሰማ ዛሬ ትዛዝ ተሰቷል።
በዚህም መሰረት ከአገር ውጭ የሚገኙት ምስክሮች ተዘጋጅተው ከግንቦት 3 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2014 ምስክርነታቸውን ለመስማት ቀጠሮ የተያዘ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ በመከላከያ ሚኒስቴር ሥር ይገኛሉ የተባሉ ምስክሮችን በተመለከተ በአካል እጀባ ተደርጎላቸው በዚሁ ቀጠሮ ቀን እንዲቀርቡ ትዛዝ መሰጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።
ሀይለማርያም ደሳለኝ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከተከሰሱበት ከዕርሻ መሳሪያ ግዢ ክስ በተጨማሪ በመርከብ ግዢ የሙስና ክስም በመከላከያ ምስክርነት የሚሰሙ መሆናቸውም ታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



