“የመንግሥት ውሳኔ ለትግራይ ክልል ብሎም ለሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወሳኝ እርምጃ ነው”፦ አሜሪካ

0
357

አርብ መጋቢት 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭት ለማቆም መወሰኑን እንደምትደግፍ እና ውሳኔውም ለትግራይ ክልል ብሎም ለሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አሜሪካ ገለፀች።

በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ማሳወቁ ይታወሳል።

ይህንም ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትናንት ባወጡት መግለጫ፤ ከትናንት ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው ይህ የመንግሥት ውሳኔን ተከትሎ የተሳለጠ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንደሚኖር ዕምነታቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን ግጭት ለማቆም መወሰኑን በአዎንታ እንደምትቀበል እና አጥብቃም እንደምትደግፍውም አስታውቀዋል።

የመንግሥት ውሳኔም ለትግራይ ክልል ብሎም ለሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወሳኝ እርምጃ እንደሆነም ተናግረዋል።

ውሳኔው በመላው ኢትዮጵያዊያን ደኅንነትና ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችል የፖለቲካ መፍትሄ ለመስጠትም መሰረት እንደሚሆንም ገልፀዋል።

አክለውም ሁሉም ወገኖች ይህንን ውሳኔ ዘላቂ የተኩስ አቁም ለማምጣት የሚያስችል ድርድርን ለማድረግ እንዲጠቀሙበት ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ ታቀርባለች ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀጣይ ሰላማዊ ጊዜን እንዲያሳልፍ አሜሪካ የቻለችውን ድጋፍ ሁሉ ማድረጓን እንደምትቀጥልም ብሊንከን በመግለጫቸው አረጋግጠዋል።

_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here