በኢትዮጵያ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ደረሰ

Views: 287

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፈው 24 ሰአታት ውስጥ በ66 ሰዎች ላይ ባደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮቪድ19 የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መኖራቸው መረጋገጡን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ይህ መረጃ እስከ ተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ በአጠቃላይ 1013 የላቦራቶሪ ምርመራ ማካሄዱን ያስታወቀ ሲሆን

በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ደርሷል፡፡

በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሁለት ግለሰቦች የ30 ዓመትና የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ በመጋቢት 15/2012 ወደ አገር የገቡ ናቸው ተብሏል።

ግለሰቦቹ በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን የበሽታውን ምልክት ታይቶባቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡

ሶስተኛዋ ታማሚ የ60 ዓመት እድሜ ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 6/2012  ከፈረንሳይ የተመለሱና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ የቆዩ ናቸው፡፡

ሶስቱም ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑም ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ አንድ ታማሚዎች ሲኖሩ ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com