ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመመከት የአለም ባንክ 82.6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቅ

Views: 209

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና በምጣኔ ኃብቷ ላይ የሚያደረስውን አደጋ ለመቀነስ የአለም ባንክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ። የባንኩ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ተጠሪ ካሮሊን ተርከ እንደገለፁት ከሆነ ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የሕብረተሰብ ጤና አገልግሎትን በማሻሻል ረገድ ውጤታማ ስራ የሰራች ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የአገሪቱን የጤና ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚፈታተነው አስታውቀዋል።
ባንኩ አገሪቷ በቫይረሱ ስርጭት የሚገጥማትን ችግር ለመቅረፍ የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ባንክ 82.6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ የባንኩ የስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ማሳለፉን በንኩ በድረገፁ ላይ አስፍሯል። ከድጋፉ ግማሹ በዝቅተኛ ወለድ የሚመለስ ብድር ሲሆን፤ ቀሪው ደግሞ ዕርዳታ መሆኑ ተጠቅሷል። ገንዘቡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ የገጠማትን ከፍተኛ የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ እንደሚረዳ ባንኩ በመግለጫው አብራርቷል።
ባንኩ የወረርሺኙን አደጋ ለመቀነስ ታዳጊ አገሮች ያለባቸውን የአቅም ችግር ለመቅረፍ 14 ቢሊዮን ደላር መድቦ እየሰራ ሲሆን፤ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚን ለመደገፍ የተቋቋመው የባንኩ አለማቀፉ የገንዘብ ኮርፖሬሽን በበኩሉ በታዳጊ አገሮች የሚገኙ ድርጅቶች በኮሮና ምክንያት የሚያጋጥማቸውን የስራ መቀዛቀዝ ተከትሎ ሰራተኞቻቸውን እንዳያሰናብቱ ለማገዝ ስምንት ቢሊዮን ዶላር መመደቡን አስታውቋል። ባንኩ በሚቀጥሉት 15 ወራት ታዳጊ አገሮች በተለይም በአፍሪካ የሚገኙ አገሮች በኮሮና ምክንያት የሚገጥማቸውን ችግር ለመቅረፍና ኢኮኖሚያቸው እንዲያገግም 160 ቢሊዮን ዶላር እንደሚለቅም ጠቅሷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 74 መጋቢት 26 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com