ለትንሳኤ በዓል ወደ እስራኤል በሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ተጥሎ የነበረው የቡድን ጉዞ እገዳ መነሳቱ ተገለጸ

0
427

አርብ መጋቢት 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ለትንሳኤ በዓል ወደ እስራኤል በሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ተጥሎ የነበረው የቡድን ጉዞ እገዳ መነሳቱን በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

የእስራኤል የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቡድን ቪዛ እገዳ መጣሉ ይታወሳል።

በዚህም ውሳኔ ቅሬታ የተሰማቸው የተለያዩ አካላት በተለይ በእየሩሳሌም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ገዳም አባቶች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት፣ ኤምባሲው ከእስራኤል ጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ ከሕዝብና ኢሚግሬሽን ጉዳይ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከተለያዩ አካላት ጋር ባደረገው ተደጋጋሚ ምክክር ውሳኔው ከኹለቱን አገራት ወዳጅነት አንጻር ተገቢ አለመሆኑን አስታውቋል።

በመቀጠልም የእስራኤል የፓርላማ አባል የሆኑት ጋዲ ይባርከን ጋር በመሆን ከእስራኤል ከሕዝብና ኢሚግሬሽን ባለስልጣን ኃላፊዎች ጋር በተደረገው ውይይት ተጥሎ የነበረው የጉዞ ገደብ የተነሳ መሆኑን በዛሬው ዕለት ኤምባሲው ገልጿል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here