የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ብቃት ያለውና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተጠቆመ

0
671

👉የመውጫ ፈተናው ከመጪው ዓመት ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ እንደሚሰጥም ተገልጿል

ሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ብቃት ያለውና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር ) ገለፁ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ጋር በመውጫ ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ አውደ ጥናት እያካሄደ ይገኛል፡፡

በአውደጥናቱ ላይ የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር ) በቀጣይ በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች ተገቢውን እውቀት ክህሎትና ሰብዕና ያሟላ ምሩቅ ለማፍራት እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

መውጫ ፈተናው በምሩቃን ፕሮፋይል መሰረት ብቁና ተወዳዳሪ ምሩቃንን በማውጣት ጥራት ያለውና በአግባቡ የሰለጠነ የሰው ሀይል ለገበያው ለማቅረብ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አቅማቸው እስኪጎለብትና አካዳሚክ እና ተቋማዊ ነጻነታቸው ሙለ በሙሉ እስኪረጋገጥ ድረሰም ፈተናው በጊዜየዊነት በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የመውጫ ፈተናው ከመጪው ዓመት ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ እንደሚሰጥ እና ለዚህም ተገቢው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here