“ዘመኑ በርካታ የግንኙነት መሣሪያ አማራጮች የበዛበት ቢሆንም ወታደራዊ ግንኙነት ግን በወታደራዊ የመገናኛ ሬዲዬ ብቻ ሊሆን ይገባል።” – ሌ/ ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ

0
834

ማክኞ መጋቢት 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) “ዘመኑ በርካታ የግንኙነት መሣሪያ አማራጮች የበዛበት ቢሆንም ወታደራዊ ግንኙነት ግን በወታደራዊ የመገናኛ ሬዲዬ ብቻ ሊሆን ይገባል።” ሲሉ የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ተናገሩ።

የደቡብ ዕዝ ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ በመሰረታዊ የግንኙነት ሙያ ያሰለጠናችውን የሠራዊት አባላት አስመርቋል።

ለሠልጣኞች የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ዘመኑ በርካታ የግንኙነት አማራጭ የበዛበት ቢሆንም ወታደራዊ አመራሩ ግንኙነቱን በወታደራዊ የመገናኛ መሳሪያ ብቻ ሊጠቀም ይገባል ብለዋል።

ባለሙያውም በክትትልና ቁጥጥር የራሱን ሚና ሊወጣ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

ሰልጣኝ የመገናኛ ባለሙያዎችም ከታች ወደ ላይ እና ከላይ ወደ ታች የሚተላለፉ መልዕክቶች ሚስጥራዊነታችውን በጠበቀ መልኩ በማሰተላለፍ ሙያዊ ግዴታችሁን መወጣትና የሠራዊቱን ግዳጅ ማገዝ ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

የዕዙ ህብረት ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ በበኩላቸው፤ ሠራዊቱን በሁሉም ዘርፍ በማሰልጠንና በማብቃት ለግዳጅ ዝግጁ የማድረግ ስራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ሠልጣኞች በቆይታቸው በመሰረታዊ የግንኙነት ሥርዓት የሚስጥር አጠባበቅና በሌሎች መሰል ዘርፎች በጉባዔና በተግባር ስልጠና ወስደው ብቃት መያዛቸውን የዕዙ ኮሙኒኬሽን ኤሌክትሮኒክስና ሳይበር መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ድሪባ ብርሃኑ በስልጠና ሪፖርታቸው ገልፀዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ለስልጠናው ስኬት አስተዋፅዖ ለነበራቸው የተለያዩ አካላት እና በውጤታቸው ብልጫ ላመጡ ሰልጣኞችም የምስጋና ምስክር ወረቀትና ሽልማት መሰጠቱን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላከታል።
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here