ማክኞ መጋቢት 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሽሮሜዳ አምባ ትምህርት ቤት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የማቾች ቁጥር ስድስት መድረሱ ተነግሯል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት፣ የማቾች ቁጥር ከዘህም ከፍ ሊል የሚችልበት አጋጣሚ አለ ብለዋል፡፡
አደጋው የደረሰው የታክሲ አገልግሎት በሚሰጥ በተለምዶ ሚኒባስ ተብሎ የሚጠራው ተሸከርካሪ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በቦታው ተገኝተው የነፍስ አድን ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ ኢንስፔክተር ማርቆስ ለራዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡
________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





