በመገናኛና አንዋር መስጊድ አካባቢ ተቋርጠዉ የነበሩት ስማርት የመኪና ማቆሚያ በድጋሚ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

0
666

ዕረቡ ሚያዝያ 5 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ በመገናኛና መርካቶ አንዋር መስጊድ አካባቢ የሚገኙ ስማርት የመኪና ማቆሚያዎች ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአዲስአበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ገለፀ፡፡

መገናኛ አካባቢ የሚገኘዉ ስማርት የመኪና ማቆሚያ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት ከሰጠ በኋላ በኤሌክትሪካል ቴክኒክ ችግር ምክንያት ተቆርጦ የነበረ ሲሆን፤ በተመሳሳይ አንዋር መስጊድ አካባቢ የተገነባው ስማርት የመኪና ማቆሚያ የኤሌክትሪክ መስመሩ በመቋረጡ አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኹለቱም ስማርት የመኪና ማቆሚያዎች ጥገና ተደርጎላቸው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል ሲል ቢሮው አስታውቋል፡፡

መገናኛ ስማርት የመኪና ማቆሚያ 90 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል ባለ 15 ደረጃ ያለው ሲሆን፤ ከአጠገቡ 105 መኪናዎችን ማስተናገድ የሚችል የመሬት ላይ መኪና ማቆሚያ አለዉ፡፡

በተመሳሳይ በአንዋር መስጊድ አካባቢ ለ80 መኪናዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል የተባለለት ስማርት የመኪና ማቆሚያዉ በመሬት ላይ ደግሞ 110 መኪናዎችን የመያዝ አቅም አለው፡፡

መኪና ማቆሚያዎቹ ለመዲናዋ ብሎም ለአገሪቱ አዲስና በዓይነታቸው የመጀመሪያ የሆኑ በቴክኖሎጂ የታገዙ መሆናቸዉ ተገልጿል።

በዚህም የከተማዋን የትራንስፖርት ሥርዓት ለማዘመን ከመሬት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ በመዲናዋ አዲስ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ ለውጥ እንዲያመጡ ታስበው የተገነቡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡
________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here